ከዚህ ህይወት በኋላ ምንድነው? ያግኙ!
Francais Español Pусский العربية Nederlands Deutsch Persian (Farsi) فارسی Bengali বাংলা Hindi हिन्दी Punjabi ਪੰਜਾਬੀ English Portugese Ukranian አማርኛ (Amharic) 简体中文 پښتو 日本語
አበባዎች በሚያምር ሁኔታ የሚያብቡ ሲሆኑ ከዚያም በፍጥነት ይጠወልጋሉ፡፡ ህይወት እንደጠዋት ጉም ነው፡፡ ለጥቂት ጊዜ የሚኖር ሲሆን ከዚያም ይሄዳል፡፡ ልክ እንደ አበባ ህይወት አንድ ቀን ያልፋል፡፡
ቀጣይ ምንድነው?
ወደፊት ሞታችን እርግጥ ነው፡፡ ከዚያ ምን ይከሰታል? እንደ አበባዎች ሳይሆን ነብሳችን በህይወት ይቆያል፡፡ በእርግጥ እግዚአብሔር እንዳለ ያስቡ፡፡ የአበባዎች እና የእርስዎ የራስዎ ፈጣሪ እንደ ሌሎች ብዙ ሰዎች እርሱን ችላ ይሉታል? ያለ እርሱ ቢሞቱ የት ሊሄዱ ይችላሉ? በእርስዎ ምን ሊከሰት ይችላል?
በምድር ላይ የህይወት ሚስጥር
ቀጭኗ ትንሽ አበባ እንኳን በሚያስደንቅ መንገድ ተይዛለች፡፡ የሰው ልጆች፣ እንስሳቶች እና ዕፅዋቶች በፍፁም መኖር እና በመሬት ምህዋር እና በዓለም አቀፍ ጠቅላላ በተወሳሰበ መዋቅር መኖራቸው አንድ ፈጣሪ መኖሩን ያረጋግጣል፡፡ እርሱም እግዚአብሔር ነው፡፡ ፍፁም ሊሆን አይችልም? በእርግጥ እርሱ ፍፁም ቅዱስ እና ሁሉን የሚችል ነው፡፡ እግዚአብሔር በእርግጠኝነት ያለ ሲሆን በየቀኑም አይኑንም በእርስዎ ላይ ከማድረግም ጭምር
የህይወታችን ውጤት
እግዚአብሔር ከእርስዎ ተመልሶ መገናኘት ይፈልጋል፡፡ አዎ፣ እርሱ በጥልቅ ፍቅር ይወድዎታል፡፡ ነገር ግን አንድ ችግር አለ፡፡ እርሱ ቅዱስ እና በህይወት ሳሉ የሚያደርጉት ስህተት ነገሮች (ኃጢአቶች) ሁሉ ከእርሱ ይለይዋችኋል፡፡ አሁን በህይወት እያሉ ብቻ ሳይሆን ኃጢአቶችዎ ከዚህ ህይወት በኋላ ገነትን እንዲያጧት ሊያደርጎት ይችላል፡፡ በኃጢአቶች ጉድፍ እና እንከን ላይ ሆነው በገነት ከቅዱስ እግዚአብሔር ጋር መኖር ለሰው ልጆች አይቻልም፡፡
የፍቅር መስዋዕትነት
እግዚአብሔር ራሱ የኃጢአቶችዎን ችግር ለመቅረፍ መርጧል፡፡ ከ 2000 ዓመት በፊት እርሱ ልጁን ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስን ወደ ምድር ልኳል፡፡ የእግዚአብሔር ብቸኛ ልጅ ኢየሱስ ክርስቶስ ለኃጢአቶችዎ ክስዎን በመውሰድ እና በመስቀል ላየ በመሞት ህይወቱን መስዋዕት አድርጓል፡፡ ይህ አስፈላጊም ነበር፡፡ ኃጢአቶችዎን ማስወገድ የሚችለው በፃድቅ ሰው ደም መፍሰስ ብቻ ነው፡፡ ከመስቀል በኋላ ኢየሱስ ክርስቶስ ከመቃብር የተነሳ ሲሆን አሁን በእግዚአብሔር ቀኝ በገነት ይኖራል፡፡ ኢየሱስ ክርስቶስ ብቻ ነው ኃጢአቶችዎን ሊያስወግድ የሚችለው፡፡ ምንም አይነት የሀይማኖት ህይወት፣ ጥሩ ስራ ወይም ምንም አይነት ነገር ሊያደርጉ ቢችሉም ወደ እግዚአብሔር ሊወስደን የሚችል መንገድ ኢየሱስ ክርስቶስ ብቻ ነው፡፡
የእግዚአብሔር ስጦታ እና ሁኔታ
በአጭሩ ይህ እውነት ነው፡፡ በመስቀሉ ሞት እግዚአብሔር ፍቅሩን የኃጢአቶችዎን ይቅርታውን፣ እና ዘላለማዊ ህይወትን ለእያንዳንዱ ሠጥቷል፡፡ ነገር ግን አንድ ሁኔታ አለ፡፡ ይህም እምነት ነው፡፡ ማንን እንመን?
- ኢየሱስ ክርስቶስ የእግዚአብሔር ልጅ እንደሆነ ይመኑ
- ኢየሱስ ክርስቶስ የኃጢአቶችዎ አዳኛ እንደሆነ ይመኑ
- ኢየሱስ ክርስቶስ የህይወትዎ ህያው ጌታ እንደሆነ በማመን ከአሁን ጀምሮ እንደ ጌታ ይቀበሉ
እንዲሁም እርሱ የሚፈልገው ሰው እንዲሆኑ እንዲያደርግ ይፍቀዱ፡፡
ይህን ሲያምኑ እና ሲናገሩ ብቻ ነው የኃጢአቶችዎን ምህረት እና ይቅርታን ሊቀበሉ የሚችሉት እና ከሞትም በኋላም የተረጋገጠ የዘላለም ህይወት በገነት ይኖርዎታል፡፡
ከኢየሱስ ክርስቶስ የተለየ ምርጫ የዘላለም ፍርድ ይዳርጋል
ምንም ነገር ወይም ከኢየሱስ ክርስቶስ ውጪ ለማመን ከመረጡ ከራሱ ከእግዚአብሔር ውጪ መሆንን መርጠዋል፡፡ ኢየሱስ ኃጢአቶችዎን እንዲያጥብልዎ እንደማይፈልጉ ካሰቡ በቀላሉ ከነ ኃጢአቶች ዕድፍዎ መቆየት እና በዚህም ምክንያት ከዚህ ህይወት በኋላ ይፈረድብናል፡፡ ውጤቱም ከእግዚአብሔር ውጪ አስቸጋሪ የዘላለም ተስፋ እና ወደ ገነት መግባት አይችልም፡፡ ይህን በደንብ ያስተውሉ!
በጊዜ ይምረጡ
ምርጫው እንደርስዎ ፍላጎት ነው፡፡ ኢየሱስ ክርስቶስን እንደ አዳኝዎ እና ጌታዎ ያምናሉ ወይስ አያምኑም? ገነትን ለማግኘት ሌላ ምንም አይነት መንገድ የለም፡፡ አሁን በምድር ላይ ሲኖሩ አዕምሯችን ለማሰራት ጊዜው አሁን ነው፡፡ ሠዎች ሳይጠበቅ ሊሞቱ ወይም አዕምሯቸውን ሊስቱ የሚችሉ ሲሆን በኢየሱስ ክርስቶስ ለማመን እና ይቅርታውን ለመጠየቅ ጠንካራ ውሳኔ ለማሳለፍ ጊዜውም ሆነ ዕድሉ አይኖረንም፡፡ ምርጫዎን አያስተላልፉ፡፡ ዛሬ የእርስዎ ቀን ነው፡፡
በመጀመርያ ከእግዚአብሔር ከራሱ ቃል እንደምንጭነት ተጨማሪ ጥልቅ መረጃ ማንበብ ከፈለጉ…
ከምንጊዜውም በላይ ምርጥ ምርጫዎችን ለማድረግ አዕምሮዎን ካሠሩት…
መልካሙን ሁሉ እንመኝልዎታለን!
ማንበብ ካልፈለጉ ለማንኛውም በአሁን ህይወት እግዚአብሔር ይባርኮት፣ ጤና እና ረጅም ዕድሜ ለእርስዎ እና ለቤተሰብዎ ይስጥዎት
ነገር ግን ስለኃጢአትዎ እና ፍርድ በማሳመን እግዚአብሔር ራሱ ከሞት በኋላ ስላለው ህይወት በልብዎ እንደሚሰራ ተስፋ እናደርጋለን፡፡
የእግዚአብሔር መንፈስ እንደ መግነጢስ ወደ ራሱ ይሳብዎት! ኢየሱስ ክርስቶስን እንደ አዳኝዎ እና ጌታዎ እንዲመርጡ በፍፁም የሚያስገድድዎት ቢሆን እንኳን በሁሉም ህይወትዎ እግዚአብሔር እንዲጎበኝዎ ወደ እርስዎ እንደሚመጣ ተስፋ እናደርጋለን፡፡
በሚያስፈልግዎ ጊዜ እንዲፀልዩ ይህን የአንድ መስመር ፀሎት በአዕምሮዎ ይያዙ
“ጌታ ኢየሱስ፣ የእግዚአብሔር ልጅ ኃጢአታችን ይቅር በል እና ነብሴን አድናት”፡፡
በህይወትዎ እግዚአብሔር ይባርኮት!