fbpx
የፀሎት ጊዜ ለእርስዎም!

የፀሎት ጊዜ ለእርስዎም!

እንኳን ደስ አለዎት!!! ጌታ ኢየሱስ ራሱ፣ አሁን በገነት የህይወትዎን ምርጥ ምርጫ የሚያጣጥሙት ትልቅ ደስታ አለ ብሏል![1]፡፡ እንደዚሁም ደግሞ መፅሀፍ ቅዱስ እንደሚለው በዚህ ምርጫ ለእግዚአብሔር ልጅ እንዲሆኑ ተሰጥተዋል[2]! አስደናቂ አይደለም?

ምርጫውን ሲያከናውኑ ሌላ ክርስቲያን ለእርስዎ አሁን መፀለይ እንደሚችሉ ሊያውቁ ይችላሉ! ለራስዎም ጥንካሬም ይፀልዩ፣ በቀረው ዘመንዎ እንዲረዳዎ እና እንዲመራዎ እግዚአብሔርን ይጠይቁ፡፡ የፀሎት ጊዜ አቅም ያለው እና አስፈላጊ የሆነ ነገር ሲሆን እንደዚሁም ደግሞ እግዚአብሔር እያንዳንዱን ፀሎተኛ ይሰማል!

ለእርስዎ እንፀልያለን፡ እግዚአብሔር እምነትዎን ያጠንክርልዎት፣ ወደ እርሱ ቀርበው እንዲያድጉ ይርዳዎ! ጥልቅ በሆነ እና ቅንነት በተሞላ እምነት በምንም አጋጣሚ፡ በደስታ እና በችግር ጊዜያት እንኳን ቢሆን እርሱን በማመን እግዚአብሔር ይባርክዎት! በህይወትዎ እግዚአብሔር ይባርክዎት!

የምስራቹ ፀሎተኛው ኢየሱስ ክርስቶስን ለመምረጥ የሚያደርገው ነገር ብቸኛው የመጀመርያ ደረጃ አስደሳቹ አዲስ ህይወት ነው፡፡ በጣም ምርጡ እና የተሻለው ገና ሊመጣ ነው፡፡ ስለዛ ጉዳይ ተጨማሪ እናንብብ…

ይቀጥሉ፡ አዲስ ህይወት

[1]

እላችኋለሁ፤ እንደዚሁም ንስሓ ከማያስፈልጋቸው ከዘጠና ዘጠኝ ጻድቃን ይልቅ፣ ንስሓ በሚገባ በአንድ ኀጢአተኛ በሰማይ ደስታ ይሆናል። ሉቃስ 15:7 NASV

እላችኋለሁ፤ እንደዚሁም ንስሓ በሚገባ በአንድ ኀጢአተኛ በእግዚአብሔር መላእክት ፊት ደስታ ይሆናል። ሉቃስ 15:10 NASV

[2]

በሰማያዊ ስፍራ በመንፈሳዊ በረከት ሁሉ በክርስቶስ የባረከን የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ አምላክና አባት ይባረክ፤ በፊቱ ቅዱሳንና ነውር አልባ እንድንሆን ዓለም ከመፈጠሩ አስቀድሞ በእርሱ መርጦናልና። በፍቅር፣ በኢየሱስ ክርስቶስ ልጆቹ እንሆን ዘንድ፣ እንደ በጎ ፈቃዱ አስቀድሞ ወሰነን፤ ይኸውም፣ በሚወደው በእርሱ በኩል በነጻ የተሰጠን ክቡር የሆነው ጸጋው እንዲመሰገን ነው። በእርሱም እንደ እግዚአብሔር ጸጋ ባለጠግነት መጠን፣ በደሙ በተደረገ ቤዛነት፣ የኀጢአትን ይቅርታ አገኘን፤ ኤፌሶን 1:3-7 NASV

የእግዚአብሔር ልጆች ተብለን እንድንጠራ አብ አትረፍርፎ ያፈሰሰልን ፍቅር ምንኛ ታላቅ ነው! እኛም እንዲሁ ልጆቹ ነን። ዓለም እኛን የማያውቀንም እርሱን ስላ ላወቀው ነው። 1 ዮሐንስ 3:1 NASV

በእግዚአብሔር መንፈስ የሚመሩ እነዚህ የእግዚአብሔር ልጆች ናቸውና። እንደ ገና የፍርሀት ባሪያ የሚያደርጋችሁን መንፈስ ሳይሆን፣ “አባ፣ አባት” ብለን የምንጠራበትን የልጅነት መንፈስ ተቀብላችኋልና፤ የእግዚአብሔር ልጆች መሆናችንን ያ መንፈስ ራሱ ከመንፈሳችን ጋር ሆኖ ይመሰክርልናል። ልጆች ከሆን ወራሾች ደግሞ ነን፤ የክብሩ ተካፋዮች እንሆን ዘንድ በርግጥ የመከራው ተካፋዮች ብንሆን፣ የእግዚአብሔር ወራሾች፣ ከክርስቶስ ጋር አብረን ወራሾች ነን። ሮሜ 8:14-17 NASV

ይኸውም በጠማማና በክፉ ትውልድ መካከል ንጹሓንና ያለ ነቀፋ፣ ነውርም የሌለባቸው የእግዚአብሔር ልጆች ሆናችሁ፣ እንደ ከዋክብት በዓለም ሁሉ ታበሩ ዘንድ ነው። ፊልጵስዩስ 2:15 NASV

ልጆችም ስለ ሆናችሁ እግዚአብሔር፣ “አባ አባት” ብሎ የሚጮኽ የልጁን መንፈስ ወደ ልባችን ላከ።
ገላትያ 4:6 NASV

[3]

ስለዚህ ኀጢአታችሁን እርስ በርሳችሁ ተናዘዙ፤ ትፈወሱም ዘንድ አንዱ ለሌላው ይጸልይ። የጻድቅ ሰው ጸሎት ኀይል አለው፤ ታላቅ ነገርም ያደርጋል። ያዕቆብ 5:16 NASV