ስለ

ስለ

ለምንድነው ሰዎች አበባዎችን የሚበልጡት?

ሠዎች ልክ እንደ አበባዎች ናቸው፡ የምንኖረው እና የምናብበው ለአጭር ጊዜ ሲሆን ከዚያም ህይወት ያበቃል፡፡ ነገር ግን በእውነት ይህ እውነት ነው? ህይወት ከሞት በኋላ በቀላሉ ያበቃል ወይስ ተጨማሪ ሌላ ይኖራል? ውስጣዊ ማንነትዎ፣ ነፍስዎ፣ ከህይወት በኋላ ምን ሊሆን ይችላል?

www.flowerexcel.com ድህረ ገፅ አሁን ከእግዚአብሔር ሰላምን የምናገኝበትን መንገድ እና ከዚህ ህይወት በኋላ በገነት የዘላለም ህይወት እንዴት እንደምናገኝ ለማሳየት ጥረት ያደርጋል፡፡ እንዴት እግዚአብሔር እውነተኛ እና እንዴት እርሱን ማግኘት እንደሚቻል ይማሩ፡፡ እንዴት እርስዎ ለእግዚአብሔር ትልቅ ዋጋ ያለዎት እንደሆኑ እና እንዴት እርሱ ፍቅሩን እንደገለፀልዎ ያንብቡ፡፡

ተመልሶ ለመገናኘት ከእግዚአብሔር ጋር ግንኙነት ለማድረግ እንዴት እንደሚቻል፣ በህይወትዎ በሁሉም ነገሮች ለሠሩት ስህተቶች ይቅርታን እንዴት እንደሚቀበሉ ይፈልጉ፡፡ በተስፋ እና ለወደፊት አዲስ እና የሚያምር ህይወት፣ እንዴት እንደሚጀምሩ ይማሩ፡፡

ተልዕኳችን

የ flowerexcel  ድህረ ገፅ ሠዎች በልባቸው ውስጥ እውነተኛ ሠላም የሚያገኙበትን መንገድ፣ ለስህተቶችዎ ይቅርታን እንዴት እንደሚቀበሉ እና ህይወት ከተፈፀመ በኋላ በገነት የዘላለም ህይወት እንዴት እንደሚኖሩ የማሳየት ተልዕኮ አለው፡፡ የ flowerexcel በዓለም ላይ ያሉ ጎብኝዎችን በህይወት ውስጥ ያለውን ዓላማ እና ፍቺዎችን እንዲያገኙ መርዳት ይፈልጋል፡፡

የ flowerexcel ቡድን ይህን መንፈሳዊ እርዳታ የሚሰጠውን ድህረ ገፅ ለመያዝ የሚሳተፍ ብቻ ሳይሆን በብዙ እስያ እና አፍሪካ ሀገራት ውስጥ በአካባቢያዊ ፕሮጀክቶች ሠዎችን ለመርዳት የመሠረት ክፍል ነው፡፡ እነዚህም ፕሮጀክቶች ትምህርት፣ አሳዳጊ የሌላቸውን ልጆች እና የሊፕረሲ እርዳታ እና ሌሎችም ናቸው፡፡ የስራ ማስኬጃ ወጪዎችን ለመቀነስ ሁሉም የአስተዳደር ስራዎች የሚከናወኑት ፍቃደኛ በሆኑ ሰዎች ነው፡፡

የመገናኛ አድራሻ

ወደ የፖ. ሳጥን 39F, 2140 AA Vijfhuizen, ሆላንድ የፖስታ መልዕክት በመላክ የ flowerexcel ማግኘት ይቻላል፡፡ Flowerexcel በ Facebook እና በ Instagram ሊያገኙ ይችላሉ፡፡