የተጠሙ አበባዎች
እያንዳንዱ አበባዎች ውሀ እንደሚፈልጉ ያውቃል፡፡ ነገር ግን አንዳንድ ጊዜ እኛ ሠዎች እንደተጠሙ አበባዎች ሊሰማን ይችላል፡፡
ህይወትዎ ልክ እንደዚህ ከሆነ …..
- በማደግ ላይ ያለ…
- ትምህርት ጨርሰው ትምህር ወይም ከትምህርት ውጪ…
- ህይወትዎን ስለመውደድ ሲመለከቱ
- እርሱን/እርሷን ለማግኘት እድለኛ ሊሆኑ ስለሚችሉ
- ልጆች ሊኖርዎት ወይም ላይኖርዎት
- በየቀኑ ህይወትዎ በመስራት እና አሁን ደግሞ በማርጀት ላይ መሆንዎ…
- ጡረታ እስከሚወጡ ድረስ ሠርተው ከሆነ…
- በተለያዩ ቦታዎች በመጓዝ ወይም በእርጅናዎ ጊዜ በቤትዎ መደሰት…
ከዚያም ህይወት ያበቃል?
ህይወት ምንም ያህል ሊሆን ቢችልም የሆነ ቦታ ይህ ሀሳብ አዕምሮዎን ተሻግሮ ሊሄድ ይችላል፡፡ “ይህ ሁሉ በህይወት ውስጥ አለ?” …
አይደለም፣ በህይወት ውስጥ ተጨማሪ ነገር አለ!
ታዋቂው ፈላስፋ ብሌይዝ ፓስካል በመፅሀፉ ፔንሲስ ፅፏል፡፡
“ ይህ ከፍ ያለ ፍላጎት፣ እና ይህ ተስፋ መቁረጥ፣ የሚገልፁ ነገር ግን በሰው ውስጥ አንድ ጊዜ እውነተኛ ደስታ እንደነበር ከእነዚህ ውስጥ አሁን በባዶ ዕትም እና መንገድ ላይ የቀሩት ምንድናቸው? ይህ አጠገብ ባለው ማንኛውም ነገር ለመሙላት መሞከር፣ የሌሉ ነገሮችን በመፈለግ ምንም እንኳን ማንም ሊረዳ የሚችል የሌለውን ማግኘት የማይቻለውን እርዳታ መሻት፣ ይህ ማለቂያ የሌለው ገደላማ ቦታ ሊሞላ የሚችለው ማለቂያ በሌለው የማይለወጥ ነገር ብቻ ሲሆን በሌላ አነጋገር በእግዚአሔር በራሱ ነው”፡፡
ቀለል አድርጎ ለመግለፅ በህይወት ውስጥ የተሟላ እና እውነተኛ ደስታን ለማግኘት ለእግዚአብሔር በህይወትዎ ውስጥ ክፍል ከሠሩ ነው፡፡ እግዚአብሔር እርሱን እንዲያውቁት ለማድረግ የተሟላ እንዲሆን ይወዳል፡፡
የተረጋጋ ንፁህ ውሀ
ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ይህን ውስጣዊ ፍላጎት ከመራብ እና መጠማት ጋር ያነፃፅረዋል፡፡ በህይወቱ ውስጥ ተጨማሪ ነገር እንዲመጣ ውስጣዊ መራብ እና መጠማት ላለው ማንኛውም ሠው ይጋብዛል[1] ፡፡ ሙሉ ለሙሉ የሚያረካው መንፈሳዊ ጥማትዎን ብቻ ሳይሆን፣ እጅግ ለሰው በጣም ብዙ የሆነውን እና ለሌሎችም የሚያጋሩት የህይወት ውሀ እንዲኖርዎት ይፈልጋል[2] ፡፡ ምን እንደሆነ ይገምቱ፣ ይህ የህይወት ውሀ እንኳን በነፃ ነው[3]!
እንሂድ እና ፍለጋውን እንጀምር[4]!
[1]
ለሚጠፋ እንጀራ አትሥሩ፤ ነገር ግን የሰው ልጅ ለሚሰጣችሁ ለዘላለም ሕይወት ለሚኖር ምግብ ሥሩ፤ ለዚህም እግዚአብሔር አብ ማረጋገጫ ማኅተሙን በእርሱ ላይ አትሞአልና።” ዮሐንስ 6:27 NASV
ኢየሱስም እንዲህ አላቸው፤ “የሕይወት እንጀራ እኔ ነኝ፤ ወደ እኔ የሚመጣ ከቶ አይራብም፤ በእኔም የሚያምን ፈጽሞ አይጠማም። ዮሐንስ 6:35 NASV
የበዓሉ መጨረሻ በሆነው በታላቁ ቀን፣ ኢየሱስ ቆሞ ከፍ ባለ ድምፅ እንዲህ አለ፤ “ማንም የተጠማ ቢኖር ወደ እኔ ይምጣና ይጠጣ፤ ዮሐንስ 7:37 NASV
[2]
እኔ ከምሰጠው ውሃ የሚጠጣ ግን ከቶ አይጠማም፤ እኔ የምሰጠው ውሃ በውስጡ የሚፈልቅ የዘላለም ሕይወት ውሃ ምንጭ ይሆናል።” ዮሐንስ 4:14 NASV
በእኔ የሚያምን፣ መጽሐፍ እንዳለ የሕይወት ውሃ ምንጭ ከውስጡ ይፈልቃል።” ዮሐንስ 7:38 NASV
[3]
እናንት የተጠማችሁ ሁሉ ኑ፤ እናንት ገንዘብ የሌላችሁ፣ ወደ ውሆች ኑ፤ ኑና ግዙ፤ ብሉም፤ ኑና ያለ ገንዘብ፣ ያለ ዋጋ፣ የወይን ጠጅና ወተት ግዙ። ገንዘባችሁን እንጀራ ባልሆነ ነገር ላይ ለምን ታጠፋላችሁ? በማያጠግብስ ነገር ላይ ለምን ጒልበታችሁን ትጨርሳላችሁ? ስሙ፤ እኔን ስሙኝ፤ መልካም የሆነውንም ብሉ፤ ነፍሳችሁም በጥሩ ምግብ ትደሰታለች። ጆሮአችሁን ከፍታችሁ ወደ እኔ ቅረቡ፤ ነፍሳችሁም እንድትኖር አድምጡኝ። ለዳዊት በገባሁት በጽኑ ፍቅሬ፣ ከእናንተም ጋር የዘላለም ኪዳን አደርጋለሁ። ኢሳይያስ 55:1-3 NASV
[4]
ነገር ግን እዚያም ሆናችሁ አምላካችሁን እግዚአብሔርን (ኤሎሂም ያህዌ) በፍጹም ልባችሁና በፍጹም ነፍሳችሁ ብትፈልጉት ታገኙታላችሁ። ዘዳግም 4:29 NASV
እናንተ ትፈልጉኛላችሁ፣ በፍጹም ልባችሁም ከፈለጋችሁኝ ታገኙኛላችሁ፤ ኤርምያስ 29:13 NASV
የሚወዱኝን እወዳቸዋለሁ፤ ተግተው የሚሹኝም ያገኙኛል። ምሳሌ 8:17 NASV
“ለምኑ፣ ይሰጣችኋል፤ ፈልጉ፣ ታገኛላችሁ፤ አንኳኩ፣ በሩም ይከፈትላችኋል። የሚለምን ሁሉ ይሰጠዋል፤ የሚፈልግም ያገኛል፤ ለሚያንኳኳም በሩ ይከፈትለታል። ማቴዎስ 7:7-8 NASV
“ስለዚህ እላችኋለሁ፤ ለምኑ ይሰጣችኋል፤ ፈልጉ ታገኛላችሁ፤ በር አንኳኩ ይከፈትላችኋል፤ ምክንያቱም የሚለምን ሁሉ ይቀበላል፤ የሚፈልግም ያገኛል፤ በር ለሚያንኳኳም ይከፈትለታል። ሉቃስ 11:9-10 NASV
እግዚአብሔር በሚገኝበት ጊዜ ፈልጉት፤ ቀርቦም ሳለ ጥሩት። ኢሳይያስ 55:6 NASV