ጠቃሚ ማስፈንጠርያዎች

ጠቃሚ ማስፈንጠርያዎች

ከዚህ በታች ማስፈንጠርያዎች አሉ፤ መጀመርያ ይህንን፣

እንደገናም እርሱ (ጌታ ኢየሱስ) በባህር ማስተማር ጀምሯል፡፡ እናም በጣም ብዙ በርካታ ሠዎች ወደ እርሱ ተሰብስበው የነበረ ሲሆን እርሱም በባህሩ ላይ ወደ ጀልባዋ ውስጥ በመግባት ተቀመጠ፡፡ እናም ሁሉም የተሰበሰቡት በርካታ ሠዎች በባህሩ ፊት ለፊት መሬት ላይ ነበሩ፡፡ ከዚያም ብዙ ነገሮችን በምሳሌያዊ አነጋገሮች በማስተማር እንደዚህ አላቸው፡፡

“አድምጡ፣ እነሆ ገበሬው ዘር ሊዘራ ወጣ፡፡ በሚዘራበት ጊዜ አንዳንድ ዘሮች በመንገድ ዳር ላይ ወደቁ፡፡ ወፎችም ከአየር ላይ መጥተው ለቀሟቸው፡፡ አንዳንዶቹም በድንጋያማ መሬት ላይ ወደቁ፤ እዚያም በቂ አፈር አላገኙም፡፡ ወደ መሬት ጥልቀት ስለሌላቸው ወዲያው አደጉ፡፡ ነገር ግን ፀሀይ ሲወጣ ተለበለቡ፡፡ ከዚያም ስር ስለሌላቸው ጠወለጉ፡፡ እንዳዶች ደግሞ በእሾኻማ መሀል ወደቁ፡፡ እሾኾቹም ያደጉትን አንቀው ያዟቸው፡፡ ከዚያም በውጤቱም ምንም ያክል ሳያፈሩ ቀሩ፡፡ ነገር ግን ሌሎቹ ዘሮች በጥሩ መሬት ላይ ወደቁ፡፡ በውጤቱም ጥሩ ተከል የሚያድጉ እና የሚያፈሩ ሆኑ፡፡ አንዳንዶቹ ሰላሳ እጥፍ፣ ሌሎቹ ስልሳ እጥፍ፣ ቀሪዎቹ መቶ እጥፍ አፈሩ፡፡

ከዚያም እንደዚህ አላቸው “ጆሮ ያለው ይስማ”

ነገር ግን ብቻውን ሲሆን አብረውት ያሉት አስራሁለቱ ስለምሳሌያዊ አነጋገሩ ጠየቁት፡፡ እሱም መለሰላቸው፡፡ “ለእናንተ የእግዚአብሔር መንግስት ሚስጥር እንድታውቁ ተሰጥቷችኋል፡፡ ነገር ግን ለሌሎች ውጭ ላሉት ሁሉም ነገሮች በምሳሌያዊ አነጋገሮች ነው የሚመጡት፣ ስለዚህም

ማየትን ያያሉ ግን አይመለከቱም

መስማትን ይሰማሉ ነገር ግን አያዳምጡም

እስኪመለሱ ድረስ

ኃጢአታቸውን ይቅር ይላቸዋል፡፡

በሌላ ጊዜ ደግሞ በባሕሩ አጠገብ ያስተምር ጀመር። እርሱ ባለበት አካባቢ እጅግ ብዙ ሕዝብ ስለ ተሰበሰበ፣ በባሕሩ ላይ ወዳለች ጀልባ ገብቶ ተቀመጠ፤ ሕዝቡም ሁሉ በባሕሩ ዳርቻ ባለው ስፍራ ላይ ተሰብስቦ ነበር። እርሱም ብዙ ነገሮችን በምሳሌ አስተማራቸው፤ እንዲህም አላቸው፤ “ስሙ፤ አንድ ዘሪ ዘር ሊዘራ ወጣ። ዘሩን በሚዘራበትም ጊዜ አንዳንዱ መንገድ ላይ ወደቀ፤ ወፎችም መጥተው ለቅመው በሉት። ሌላው በቂ ዐፈር በሌለበት በጭንጫ ቦታ ላይ ወደቀ፤ ዐፈሩ ጥልቀት ስላልነበረው ወዲያው በቀለ፤ ፀሓይ በወጣ ጊዜ ግን ጠወለገ፤ ሥር ስላልነበረውም ደረቀ። ሌላው ዘር ደግሞ በእሾኽ መካከል ወደቀ፤ እሾኹም አድጎ የዘሩን ተክል ስላነቀው ፍሬ አላፈራም። ሌላው ዘር ደግሞ በመልካም መሬት ላይ ስለ ወደቀ በቅሎ አደገ፤ ፍሬም ሰጠ፤ አንዱ ሠላሣ፣ አንዱ ሥልሳ፣ ሌላውም መቶ ፍሬ አፈራ።” ቀጥሎም ኢየሱስ፣ “የሚሰማ ጆሮ ያለው ይስማ” አለ። ብቻውን በሆነ ጊዜ፣ ዐሥራ ሁለቱና አብረውት የነበሩት ሌሎች ስለ ምሳሌዎቹ ጠየቁት። እርሱም፣ “ለእናንተ የእግዚአብሔር መንግሥት ምስጢር ተሰጥቶአችኋል፤ በውጭ ላሉት ግን ነገር ሁሉ በምሳሌ ይነገራቸዋል፤ ይኸውም፣ ‘ማየቱን እንዲያዩ እንዳያስተውሉትም፣ መስማቱን እንዲሰሙ ልብ እንዳይሉትም፣ እንዳይመለሱና ኀጢአታቸው እንዳይሰረይላቸው ነው’ አላቸው።” ከዚያም ኢየሱስ እንዲህ አላቸው፤ “ይህን ምሳሌ አልተረዳችሁትምን? ታዲያ ሌሎቹን ምሳሌዎች ሁሉ እንዴት ልትረዱ ትችላላችሁ? ዘሪው ቃሉን ይዘራል። አንዳንድ ሰዎች በመንገድ ላይ የወደቀውን ዘር ይመስላሉ፤ ቃሉን በሚሰሙበት ጊዜ ሰይጣን ወዲያውኑ መጥቶ በውስጣቸው የተዘራውን ቃል ይወስደዋል። እንዲሁም ሌሎች በጭንጫ ቦታ ላይ የተዘራውን ዘር ይመስላሉ፤ ቃሉን በሚሰሙበት ጊዜ ወዲያው በደስታ ይቀበሉታል፤ ነገር ግን ሥር የሌላቸው ስለሆኑ የሚቈዩት ለጥቂት ጊዜ ብቻ ነው፤ በቃሉ ምክንያት መከራ ወይም ስደት በመጣ ጊዜ ወዲያውኑ ይሰናከላሉ። ሌሎቹ ደግሞ በእሾኽ መካከል የተዘራውን ዘር ይመስላሉ፤ ቃሉን መስማት ይሰማሉ፤ ነገር ግን የዚህ ዓለም ውጣ ውረድ፣ የሀብት አጓጊነት እንዲሁም የሌሎች ነገሮች ምኞት ቃሉን አንቀው በመያዝ ፍሬ እንዳ ያፈራ ያደርጉታል። ሌሎቹ በመልካም መሬት ላይ የተዘራውን ዘር ይመስላሉ፤ እነዚህም ቃሉን ሰምተው የሚቀበሉና ሠላሳ፣ ሥልሳ፣ መቶም ፍሬ የሚያፈሩ ናቸው።” ማርቆስ 4:1-20 NASV

ፍሬያማ መሆን

ጌታ ኢየሱስን እንደ አዳኝዎ እና ጌታዎ ለመከተል ምርጫ አድርገዋል? ያ በጣም ድንቅ ነው! አሁን እንዴት ህይወትዎ ይቀጥል?

እንደገና ወዲያው ይረሳሉ?

በደስታ ከተቀበሉት በኋላ ለጥቂት ጊዜ ብቻ ነው የሚታገሱት እናም ችግሮች ሲጠነክሩ ወዲያው ይሠናከላሉ?

ጭንቀት፣ ስግብግብነት ወይም ሀብታምነት እንዲወጥርዎ በመፍቀድ እንዲረሱ ያደርግዎታል?

ወይም ህይወትዎ ፍሬያማ፣ ብዙ ፍሬ ያዘሉ ይሆናሉ፡፡ ተስፋ እናደርጋለን፣ በእርግጥ ጥሩ አማራጭ ስለሆነ

በመጨረሻው ምድብ መሆንዎን እና ሁልጊዜ ለጌታ የቀረቡ መሆንዎን ያረጋግጡ፡፡

ጥሩ ቤተክርስቲያን፣  የሌሎች ቤተክርስቲያን ቡድንን እንዲያገኙ አበክረን እየመከርንዎት ቤተክርስቲያን ጌታ ኢየሱስ ዋናው ነጥብ የሆነበት እና ሠዎች አማኝ እና እንደ መፅሀፍ ቅዱስ የሚኖሩበት ቦታ ነው፡፡ ይህም በእምነትዎ እንዲያድጉ ድጋፍ እና እርዳታ ይሠጥዎታል፡፡ አንድ ቀን ሽልማቱ ስለሚሰጥዎት በዚህ ህይወት በጌታ ኢየሱስ ተስፋ እንዳይቆርጡ!

ድህረ ገፆች

የሚከተሉት ድህረ ገፆች እርስዎን የሚረዱ ጥሩ ናቸው

www.alpha.org (ስለ መሰረታዊ ነገር ተጨማሪ)

www.biblegateway.com (መፅሀፍ ቅዱስ በብዙ ቋንቋዎች)

www.youversion.com (መፅሀፍ ቅዱስን በቀጥታ ኢንተርኔት፣ በብዙ ቋንቋዎች)

http://christianpf.com/free-bible (ነፃ መፅሀፍ ቅዱስ እንዴት እንደምንቀበል)

http://bibleseo.com/free-bible-studies/ (የመፅሀፍ ቅዱስ ጥናት)

www.gracethrufaith.com  (ስለመፅሀፍ ቅዱስ እና የመፅሀፍ ቅዱስ ጥናት ተጨማሪ በጣም የሚስቡ ጥያቄም መጠየቅም ይቻላል)

isaalmasih.net (ተጨማሪ መረጃዎች በአረብኛ፣ ኢንዶኔዥያ፣ ቱርክ፣ ስፔን፣ እና ፖርቱጋል)

ar.arabicbible.com/ (ተጨማሪ መረጃ በአረብኛ)

www.cru.org (ከሌሎች እምነትዎን እንዴት እንደሚያካፍሉ)

ፊልም

ይህ ፊልም ለማየት ጥሩ ነው

  • ስለ ኢየሱስ ፊልም (ከ 1000 ቋንቋዎች በላይ ይገኛል)
  • በአይፎን መተግበርያ ወይም በአንድሮይድ መተግበርያ ለመመልከት ይቻላል

ጥያቄዎች ሲኖርዎ

በነዚህ ድህረ ገፆች ተጨማሪ ማንበብ ብቻ ሳይሆን ጥያቄዎችዎን ይጠይቃሉ፡፡

ኢየሱስ ክርስቶስ እንደ አዳኝዎ እና ጌታዎ ምርጫዎ ካደረጉ እና አድርገን እንደነበረው ጌታ ኢየሱስ ዘላለማዊ ህይወት ሊሰጠን ቃል ስለገባልን በእርግጠኝነት በገነት እንገናኛለን፡፡ ያችን ጊዜ እንመኛለን፡፡ ለአሁን በህይወትዎ የእግዚአብሔርን ፍቅር፣ በረከት፣ እና ጥበቃን እንመኝልዎታለን! በእምነትዎ አድገው እንዲያብቡ ይሁን!

ኢየሱስ ብሏል፡

“በእርሱ የሚያምን ሁሉ የዘላለም ሕይወት እንዲኖረው እንጂ እንዳይጠፋ እግዚአብሔር አንድያ ልጁን እስከ መስጠት ድረስ ዓለምን እንዲሁ ወዶአልና፤ ዮሐንስ 3:16 NASV

አብ በማንም ላይ አይፈርድም፤ ነገር ግን ፍርድን ሁሉ ለወልድ አሳልፎ ሰጥቶታል፤ ይኸውም፣ ሁሉ አብን እንደሚያከብሩ ወልድን ያከብሩት ዘንድ ነው፤ ወልድን የማያከብር፣ የላከውን አብንም አያከብርም። “እውነት እላችኋለሁ፤ ቃሌን የሚሰማ፣ በላከኝም የሚያምን የዘላለም ሕይወት አለው፤ ከሞት ወደ ሕይወት ተሻገረ እንጂ ወደ ፍርድ አይመጣም። ዮሐንስ 5:22-24 NASV

በወልድ የሚያምን ሁሉ የዘላለም ሕይወት አለው፤ በወልድ የማያምን ግን የእግዚአብሔር ቊጣ በላዩ ይሆናል እንጂ ሕይወትን አያይም።” ዮሐንስ 3:36 NASV

የአባቴ ፈቃድ ወልድን አይቶ በእርሱ የሚያምን ሁሉ የዘላለም ሕይወት እንዲኖረው ነው፤ እኔም በመጨረሻው ቀን አስነሣዋለሁ።” ዮሐንስ 6:40 NASV