የእርስዎ ክፍል ምንድነው?

የእርስዎ ክፍል ምንድነው?

ምርጫ ያድርጉ

ብዙ ሰዎች እግዚአብሔርን ለመተው እና ያለ እርሱ ኑሯቸውን ለመኖር ይመርጣሉ [1]፡፡ ሌሎች ብዙ ሰዎች በኢየሱስ ክርስቶስ [2] ላለማመን የሚመርጡ ሲሆን አንዳንድ ጊዜ ስሙን መጠቀም እንደ እርግማን ያዩታል[3]፡፡ ወደፊት ለኃጢአታቸው እና ምርጫቸው ካለፈው ገፅ ላይ እንደተገለፀው (የሚኖሩት አንድ ጊዜ ነው) ኃላፊነት ይወስዳሉ፡፡ ነገር ግን ይህ ለእርስዎ የእግዚአብሔር ምኞት አይደለም፡፡ እግዚአብሔር ሁሉንም ሰዎች እርስዎንም ጨምሮ እንዲፀፀቱ እና ወደ እርሱ እንዲመለሱ ይፈልጋል[4]፡፡

መመለስ እንዴት አስፈላጊ እንደሆነ![5] ኢየሱስ ክርስቶስ እንደ አዳኝዎ እና ጌታዎ [7] ለማመን በመምረጥ ከኃጢአቶችዎ በመፀፀት መንፈሳዊ ህይወት ያግኙ[6]! አስተውሉ ኢየሱስ የሚወዱት የገነት አባትዎን እግዚአብሔርን ለማግኘት ብቸኛው መንገድ[8]  ስለሆነ ከኃጢአቶችዎ ዕድፎች ራስዎን የነፃ ለማድረግ [9] ሌላ አማራጮች የሉም፡፡ ምንም ካላደረጉ ወይም በኢየሱስ ክርስቶስ ማመንን [10] ከተው ዘላለማዊ ተስፋው እንደጠፋው ሰው ከእግዚአብሔር ውጪ በአስፈሪው ቦታ ይሆናሉ፡፡

(የመፀሀፍ ቅዱስ ክፍል ከዚህ ገፅ በታች “የሚኖሩት አንድ ጊዜ ነው” የሚለውን ማንበብዎን ያረጋግጡ!)እንደዚህ አይነትን አጋጣሚ ለማስወገድ ምርጫዎን ያስተካክሉ! እግዚአብሔር ትልቅ ነገር እንድናደርግ አይጠይቀንም፡፡ በእርግጥ የጌታ ኢየሱስ ክርስቶስን ህይወት ለኛ መስዋዕት ያቀረበው እርሱ ሲሆን ይህም እኛን ነፃ ለማድረግ የተከፈለ ግዙፍ ዋጋ ነው[11]፡፡ በምላሹ እግዚአብሔር እኛን የሚጠይቀው…

በልጁ በኢየሱስ ክርስቶስ እንድናምን

ምንድነው በትክክል የምናምነው?

እግዚአብሔር የእርስዎ ፈጣሪ ያለ እና የሚኖር መሆኑ[12]

ኢየሱስ ክርስቶስ የእግዚአብሔር ልጅ መሆኑ [13]

ኢየሱስ ክርስቶስ ጌታ እንደሆነ፣ ለኃጢአቶቻችን እንደሞተ እና ከሞት እንደተነሳ [14]

ከኃጢአቶችዎ መጠበቅ እንደሚያስፈልግዎ [15]

ከኃጢአቶችዎ ለመዳን ኢየሱስ ክርስቶስ እንደሚያስፈልግዎ [15]

ከኃጢአቶችዎ መፀፀት እና መመለስ እንደሚያስፈልግዎ እንደ እግዚአብሔር ልጅ ኢየሱስ ክርስቶስ ተከታይ አዲስ የተለየ ህይወት ለመኖር መጀመር

እነዚህን ነገሮች ለማመን ችግር ከገጠመዎት የእግዚአብሔር ቅዱስ መንፈስ እንዲያሳይዎ እና እንዲያምኑ እንዲረዳዎ ይፀልዩ!

 ምንድነው የሚያስወጣዎት…..

አሁን ኢየሱስ ክርስቶስን እንደ አዳኝዎ እና ጌታዎ መቀበል ምንም አይነት ገንዘብ የማያስወጣ ሲሆን የዕድል መቀየርያ የፀሎት ጊዜ መናገር ብዙ ጊዜ አያስወጣዎትም፣ (የሚቀጥለውን ገፅ ይመልከቱ፣ ለትግበራ ይዘጋጁ) ይሁን እንጂ የኢየሱስ ክርስቶስ ተከታይ አዲስ ህይወት መጀመርን ማወቅ አስፈላጊ ሲሆን በእርግጥም ህይወት መቀየር ነው፡፡ ኢየሱስን እንደ አዳኝ እና ጌታ መቀበል የመኪና መዘወርያ መሪን ለእርሱ እንደመስጠት ነው፡፡ አዲስ ህይወት መጀመር፣ ከራስዎ ፈቃድ ይልቅ የእርሱን ፈቃድ መፈለግ እና ማመን ነው፡፡

ሌሎች ሰዎች ምርጫዎን ላይወዱ የሚችሉ ቢሆንም ሊጠሉዎትም ወይም ሊያሰቃዩዎትም ይችላሉ[18]፡፡ በእያንዳንዱ 100 ሚሊየን ክርስቲያን መጠላት በኢየሱስ ክርስቶስ በማመን ምክንያት ነው፡፡ የመንፈሳዊ ወይም የአካል ጉዳት ስቃይ ይደርስባቸዋል፡፡ አሁን እንኳን የኢየሱስ ክርስቶስ ተከታይ በመሆናቸው በዓለም አቀፍ ደረጃ በሰዓት 11 ክርስቲያን ይገደላሉ፡፡ ግልፅ የሆነው ስቃይ ባያጋጥምዎትም እንኳን ኢየሱስ ክርስቶስን መከተል ከመጠቃት ነፃ አይሆኑም፡፡ እንደ ሰው በጣም ቆንጆ የሚሆኑበት እግዚአብሔር የሚሰራበት ቦታዎች የሚኖሩ ሲሆኑ በህይወትዎ ልምምድ ሊጀምሩ ይችላሉ፡፡ ልክ እንደ ጥሬ አልማዝ አብለጭላጭ እንዲሆን መቆረጥ እና መቀባባት ይኖርበታል፡፡ ለማንኛውም ብዙ ሊያከፋፍልዎት ይችላል፡፡…

…ማንኛውንም ነገር ለማግኘት!

ጌታ ኢየሱስን ለመከተል የሚያስወጣዎን ከፍያለውን ከግምትእንድናስገባ ይጠይቀናል [19]፡፡ በህይወት ውስጥ ከሁሉም ሌሎች ነገሮች በጣም አስፈላጊው ነገር እርሱ በመሆኑ ራስዎን ዋጋ ያስከፍልዎታል፡፡ በተመሳሳይ ጊዜ ይህን ውሳኔ ስናሳልፍ ማንኛውንም ነገር ሊያገኙ ይችላሉ! እነዚህ ሁሉ እንቆቅልሽ ሊሆኑ ይችላሉ፡፡

ለሰው ልጆች በጣም ጥሩ የሆነ ነገር ሊያጋጥም የሚችልበት ጉዳይ ኢየሱስ ክርስቶስን ማወቅ እንደሆነ ልናረጋግጥላችሁ እንችላለን፡፡ ይህም በህይወት ውስጥ ከማንኛውም ነገር የሚበልጥ የተደበቀን ሀብት እንደ ማግኘት ነው[20] ፡፡ በጌታ ኢየሱስ ለማመን እርምጃ መጀመር አደጋ ያለው ስለመሆኑ እርግጥ ሲሆን እጅግ በጣም ከፍተኛ አደጋ የሚሆነው ይህን ባለማድረግ ነው፡፡ በዚህ ጊዜ በህይወት ውስጥ እጅግ በጣም አስፈላጊ እና ውድ የሆነውን ነገር አሁን እና ከዚህ ህይወት በኋላም ደግሞ ሊያጡት ይችላሉ፡፡

ለማመን ምርጫ ሲያደርጉ በምላሹ እግዚአብሔር የሚሰጥዎ ምን እንደሆነ እንመልከት…

ታላቅ ስጦታዎች

 

[1]

“በጠባቡ በር ግቡ፤ ወደ ጥፋት የሚወስደው መንገድ ትልቅ፣ በሩም ሰፊ ነውና፤ ብዙዎችም በዚያ ይገባሉ። ወደ ሕይወት የሚያደርሰው ግን መንገዱ ቀጭን፣ በሩም ጠባብ ነው፤ የሚገቡበትም ጥቂቶች ብቻ ናቸው። ማቴዎስ 7:13-14 NASV

[2]

እናንተ ግን፣ ሕይወት እንዲኖራችሁ ወደ እኔ መምጣት አትፈልጉም። ዮሐንስ 5:40 NASV

ኢየሱስም እንዲህ ሲል መለሳላቸው፤ “እኔ ነግሬአችሁ ነበር፤ እናንተ ግን አታምኑም፤ በአባቴ ስም የማደርጋቸው ታምራትም ስለ እኔ ይናገራሉ፤ እናንተ ግን በጎቼ ስላልሆናችሁ አታምኑም፤
ዮሐንስ 10:25-26 NASV

[3]

ከአዳም ጀምሮ ሰባተኛ የሆነው ሄኖክ ስለ እነዚህ ሰዎች እንዲህ ሲል ተንብዮአል፤ “እነሆ፤ ጌታ ከእልፍ አእላፋት ቅዱሳኑ ጋር ይመጣል፤ ይህም፣ በሰው ሁሉ ላይ ለመፍረድ እንዲሁም ዐመፀኞችን ሁሉ በክፋት መንገድ በሠሩት የዐመፅ ሥራና በክፋት በእርሱ ላይ ስለ ተናገሩት የስድብ ቃል ሁሉ አጥፊነታቸውን ይፋ ለማድረግ ነው”። ይሁዳ 1:14-15 NASV

[4]

ማንም እንዲሞት አልሻምና፣ ይላል ጌታ እግዚአብሔር፤ ወደ እኔ ተመለሱና በሕይወት ኑሩ!
ሕዝቅኤል 18:32 NASV

እንግዲህ ኀጢአታችሁ እንዲደመሰስ ንስሓ ግቡ፤ ከመንገዳችሁም ተመለሱ፤ ከጌታም ዘንድ የመታደስ ዘመን ይመጣላችኋል፤ ደግሞም አስቀድሞ ለእናንተ የተመደበውን ክርስቶስን እርሱም ኢየሱስን ይልክላችኋል። ሐዋርያት ሥራ 3:19-20 NASV

[5]

ስለዚህ እኛ የክርስቶስ እንደራሴዎች ነን፤ እግዚአብሔርም በእኛ አማካይነት ጥሪውን ያቀርባል፤ እኛም ከእግዚአብሔር ጋር ታረቁ ብለን በክርስቶስ እንለምናችኋለን። እኛ በእርሱ ሆነን የእግዚአብሔር ጽድቅ እንድንሆን፣ ኀጢአት የሌለበትን እርሱን እግዚአብሔር ስለ እኛ ኀጢአት አደረገው። 2 ቆሮንቶስ 5:20-21 NASV

ሕይወትንና ሞትን፣ በረከትንና ርግማንን በፊትህ እንዳስቀመጥሁ ዛሬ ሰማይንና ምድርን ምስክር አድርጌ እጠራብሃለሁ። እንግዲህ አንተና ልጆችህ በሕይወት እንድትኖሩ ሕይወትን ምረጥ፤ ይኸውም አምላክህን እግዚአብሔርን (ኤሎሂም ያህዌ) እንድትወድ፣ ቃሉን እንድታደምጥና ከእርሱ ጋር እንድትጣበቅ ነው። ምክንያቱም እግዚአብሔር (ያህዌ) ሕይወትህ ነው፣ ለአባቶችህ፣ ለአብርሃም፣ ለይስሐቅና ለያዕቆብ ሊሰጣቸው በማለላቸው ምድር ረጅም ዕድሜ ይሰጥሃል። ዘዳግም 30:19-20 NASV

እንግዲህ ኀጢአታችሁ እንዲደመሰስ ንስሓ ግቡ፤ ከመንገዳችሁም ተመለሱ፤ ከጌታም ዘንድ የመታደስ ዘመን ይመጣላችኋል፤ ደግሞም አስቀድሞ ለእናንተ የተመደበውን ክርስቶስን እርሱም ኢየሱስን ይልክላችኋል። ሐዋርያት ሥራ 3:19-20 NASV

[6]

ስለዚህ ኀጢአት በአንድ ሰው በኩል ወደ ዓለም እንደ ገባ ሁሉ፣ ሞትም በኀጢአት በኩል ገብቶአል፤ በዚሁ መንገድ ሞት ወደ ሰዎች ሁሉ መጣ፤ ምክንያቱም ሁሉም ኀጢአትን ሠርተዋል፤ ሮሜ 5:12 NASV

የኀጢአት ደመወዝ ሞት ነውና፤ የእግዚአብሔር ስጦታ ግን በጌታችን በክርስቶስ ኢየሱስ የዘላለም ሕይወት ነው። ሮሜ 6:23 NASV

ነገር ግን በምሕረቱ ባለጠጋ የሆነ እግዚአብሔር ለእኛ ካለው ከታላቅ ፍቅሩ የተነሣ፣ በበደላችን ሙታን ሆነን ሳለ፣ በክርስቶስ ሕያዋን አደረገን፤ የዳናችሁት በጸጋ ነው። ኤፌሶን 2:4-5 NASV

[7]

እናንተ በበደላችሁና በኀጢአታችሁ ምክንያት ሙታን ነበራችሁ፤ ኤፌሶን 2:1 NASV

[8]

ኢየሱስም እንዲህ አለው፤ “መንገዱ እኔ ነኝ፤ እውነትና ሕይወትም እኔው ነኝ፤ በእኔ በኩል ካልሆነ በቀር ወደ አብ የሚመጣ የለም። ዮሐንስ 14:6 NASV

[9]

ነገር ግን የተወሰነው ዘመን በደረሰ ጊዜ፣ እግዚአብሔር ከሴት የተወለደውን፣ ከሕግም በታች የተወለደውን ልጁን ላከ፤ ይህም የሆነው የልጅነትን መብት እናገኝ ዘንድ ከሕግ በታች ያሉትን ለመዋጀት ነው። ልጆችም ስለ ሆናችሁ እግዚአብሔር፣ “አባ አባት” ብሎ የሚጮኽ የልጁን መንፈስ ወደ ልባችን ላከ። ገላትያ 4:4-6 NASV

ሁላችሁም በክርስቶስ ኢየሱስ በማመን የእግዚአብሔር ልጆች ናችሁ፤ ገላትያ 3:26 NASV

[10]

በእምነት፣ በጸጋ ድናችኋልና፤ ይህም የእግዚአብሔር ስጦታ ነው እንጂ ከእናንተ አይደለም፤ ማንም እንዳይመካ በሥራ አይደለም፤ ኤፌሶን 2:8-9 NASV

ነገር ግን እርሱ በብርሃን እንዳለ፣ እኛም በብርሃን ብንመላለስ እርስ በእርሳችን ኅብረት አለን፤ የልጁም የኢየሱስ ክርስቶስ ደም ከኀጢአት ሁሉ ያነጻናል። 1 ዮሐንስ 1:7 NASV

ኀጢአታችንን ብንናዘዝ ኀጢአታችንን ይቅር ሊለን፣ ከዐመፃ ሁሉ ሊያነጻን እርሱ ታማኝና ጻድቅ ነው።
1 ዮሐንስ 1:9 NASV

በዘላለም መንፈስ አማካይነት ራሱን ነውር አልባ መሥዋዕት አድርጎ ለእግዚአብሔር ያቀረበው የክርስቶስ ደም ሕያው እግዚአብሔርን እንድናመልክ ኅሊናችንን ከምውት ሥራ እንዴት ይበልጥ ያነጻ ይሆን! ዕብራውያን 9:14 NASV

[11]

ከቀድሞ አባቶቻችሁ ከወረሳችሁት ከንቱ ከሆነ ሕይወት የተዋጃችሁት በሚጠፋ ነገር፣ በብር ወይም በወርቅ እንዳልሆነ ታውቃላችሁ፤ ነገር ግን እናንተ የተዋጃችሁት ነውርና እንከን እንደሌለበት በግ ደም፣ በክርስቶስ ክቡር ደም ነው። 1 ጴጥሮስ 1:18-19 NASV

[12]

ደግሞም ያለ እምነት እግዚአብሔርን ደስ ማሰኘት አይቻልም፤ ምክንያቱም ወደ እግዚአብሔር የሚቀርብ ሁሉ እግዚአብሔር መኖሩንና ከልብ ለሚሹትም ዋጋ እንደሚሰጥ ማመን አለበት።
ዕብራውያን 11:6 NASV

[13]

ኢየሱስም፣ “እርሱ በላከው ታምኑ ዘንድ፣ ይህ የእግዚአብሔር ሥራ ነው” ሲል መለሰላቸው።
ዮሐንስ 6:29 NASV

እርሷም፣ “አዎን ጌታ ሆይ፤ አንተ ወደ ዓለም የሚመጣው ክርስቶስ የእግዚአብሔር ልጅ መሆንህን አምናለሁ” አለችው። ዮሐንስ 11:27 NASV

ከዚያም ኢየሱስ ድምፁን ከፍ አድርጎ እንዲህ አለ፤ “ማንም በእኔ ቢያምን በእኔ ብቻ ሳይሆን በላከኝም ማመኑ ነው፤ ዮሐንስ 12:44 NASV

ነገር ግን ኢየሱስ እርሱ ክርስቶስ፣ የእግዚአብሔርም ልጅ እንደሆነ ታምኑ ዘንድ፣ አምናችሁም በስሙ ሕይወት እንዲኖራችሁ ይህ ተጽፎአል። ዮሐንስ 20:31 NASV

ፊልጶስም፣ “በፍጹም ልብህ ካመንህ መጠመቅ ትችላለህ” አለው። ጃንደረባውም፣ “ኢየሱስ ክርስቶስ የእግዚአብሔር ልጅ እንደሆነ አምናለሁ” ሲል መለሰለት፤ ሐዋርያት ሥራ 8:37 NASV

[14]

“ኢየሱስ ጌታ ነው” ብለህ በአፍህ ብትመሰክር፣ እግዚአብሔርም ከሙታን እንዳስነሣው በልብህ ብታምን፣ ትድናለህ። የምትጸድቀው በልብህ አምነህ ነው፤ የምትድነውም በአፍህ መስክረህ ነውና።
ሮሜ 10:9-10 NASV

እኔ የተቀበልሁትንና ከሁሉ በላይ የሆነውን ለእናንተ አስተላልፌአለሁ፤ ቅዱሳት መጻሕፍት እንደሚሉት ክርስቶስ ስለ ኀጢአታችን ሞተ፤ ተቀበረ፤ በቅዱሳት መጻሕፍት እንደ ተጻፈውም በሦስተኛው ቀን ተነሣ፤ ከዚያም ለኬፋ ታየ፤ ቀጥሎም ለዐሥራ ሁለቱ ታየ፤ ከዚያም በኋላ ከአምስት መቶ በላይ ለሚሆኑ ወንድሞች በአንድ ጊዜ ታየ፤ ከእነዚህም አብዛኛዎቹ በሕይወት አሉ፤ አንዳንዶቹ ግን አንቀላፍተዋል። 1 ቆሮንቶስ 15:3-6 NASV

ከስምንት ቀን በኋላም፣ ደቀ መዛሙርቱ በቤት ውስጥ ነበሩ፤ ቶማስም ከእነርሱ ጋር ነበር፤ በሮቹ ተቈልፈው ነበር፤ ኢየሱስ ግን መጥቶ በመካከላቸው ቆመና፣ “ሰላም ለእናንተ ይሁን” አላቸው። ከዚያም ቶማስን፣ “ጣትህን ወደዚህ አምጣ፤ እጆቼንም ተመልከት፤ እጅህን ዘርጋና በጐኔ አስገባ፤ አትጠራጠር፤ እመን” አለው። ቶማስም፣ “ጌታዬ፤ አምላኬም!” አለው። ኢየሱስም፣ “አንተ ስላየኸኝ አምነሃል፤ ሳያዩ የሚያምኑ ግን ብፁዓን ናቸው” አለው። ዮሐንስ 20:26-29 NASV

[15]

እኔም ኀጢአተኞችን ወደ ንስሓ ልመልስ እንጂ ጻድቃንን ልጠራ አልመጣሁም።” ሉቃስ 5:32 NASV

ነገር ግን በደላችሁ ከአምላካችሁ ለይቶአችኋል፤ ኀጢአታችሁ ፊቱን ከእናንተ ሰውሮታል፤ በዚህም ምክንያት አይሰማም። ኢሳይያስ 59:2 NASV

እናንተ በበደላችሁና በኀጢአታችሁ ምክንያት ሙታን ነበራችሁ፤ ኤፌሶን 2:1 NASV

እንግዲህ ኀጢአታችሁ እንዲደመሰስ ንስሓ ግቡ፤ ከመንገዳችሁም ተመለሱ፤ ከጌታም ዘንድ የመታደስ ዘመን ይመጣላችኋል፤ ሐዋርያት ሥራ 3:19 NASV

እንዲሁም ታማኝ ምስክር፣ ከሙታን በኵርና የምድር ነገሥታት ገዥ ከሆነው ከኢየሱስ ክርስቶስም ጸጋና ሰላም ለእናንተ ይሁን። ለወደደንና ከኀጢአታችንም በደሙ ነጻ ላወጣን፣ ራእይ 1:5 NASV

[16]

ድነት በሌላ በማንም አይገኝም፤ እንድንበት ዘንድ ለሰዎች የተሰጠ ከዚህ ስም በስተቀር ሌላ ስም ከሰማይ በታች የለምና።” ሐዋርያት ሥራ 4:12 NASV

ኢየሱስም እንዲህ አለው፤ “መንገዱ እኔ ነኝ፤ እውነትና ሕይወትም እኔው ነኝ፤ በእኔ በኩል ካልሆነ በቀር ወደ አብ የሚመጣ የለም። ዮሐንስ 14:6 NASV

እነርሱም፣ “በጌታ በኢየሱስ እመን፤ አንተም ቤተ ሰዎችህም ትድናላችሁ” አሉት። ሐዋርያት ሥራ 16:31 NASV

[17]

እንግዲህ ኀጢአታችሁ እንዲደመሰስ ንስሓ ግቡ፤ ከመንገዳችሁም ተመለሱ፤ ከጌታም ዘንድ የመታደስ ዘመን ይመጣላችኋል፤ ደግሞም አስቀድሞ ለእናንተ የተመደበውን ክርስቶስን እርሱም ኢየሱስን ይልክላችኋል።
ሐዋርያት ሥራ 3:19-20 NASV

እኔም ኀጢአተኞችን ወደ ንስሓ ልመልስ እንጂ ጻድቃንን ልጠራ አልመጣሁም።” ሉቃስ 5:32 NASV

ከዚያም ኢየሱስ ደቀ መዛሙርቱን እንዲህ አላቸው፤ “ሊከተለኝ የሚወድ ራሱን ይካድ፣ መስቀሉንም ተሸክሞ ይከተለኝ፤ ማቴዎስ 16:24 NASV

እንግዲህ እንደ ተወደዱ ልጆች እግዚአብሔርን ምሰሉ፤ ክርስቶስ እንደ ወደደን ራሱንም ስለ እኛ መልካም መዐዛ ያለው መባና መሥዋዕት አድርጎ ለእግዚአብሔር እንደ ሰጠ እናንተም በፍቅር ተመላለሱ። ኤፌሶን 5:1-2 NASV

[18]

ዓለም እናንተን ሊጠላ አይችልም፤ እኔ ግን፣ አድራጎቱ ክፉ መሆኑን ስለምመሰክርበት ይጠላኛል።
ዮሐንስ 7:7 NASV

“ዓለም ቢጠላችሁ፣ ከእናንተ በፊት እኔን እንደ ጠላኝ ዕወቁ። ከዓለም ብትሆኑ ኖሮ፣ ዓለም የራሱ እንደሆኑት አድርጎ በወደዳችሁ ነበር፤ ከዓለም ለይቼ ስለ መረጥኋችሁ የዓለም አይደላችሁም፤ ዓለም የሚጠላችሁም ስለ ዚሁ ነው። ዮሐንስ 15:18-19 NASV

ቃልህን ሰጥቻቸዋለሁ፤ እኔ ከዓለም እንዳይደለሁ፣ እነርሱም ከዓለም ባለመሆናቸው ዓለም ጠልቶአቸዋል። ዮሐንስ 17:14 NASV

ወንድሞች ሆይ፤ ዓለም ቢጠላችሁ አትደነቁ። 1 ዮሐንስ 3:13 NASV

‘ክርስቶስ ኢየሱስ ኀጢአተኞችን ለማዳን ወደ ዓለም መጣ’ የሚለው ቃል እውነተኛና ሰው ሁሉ ሊቀበለው የሚገባ ነው፤ ከኀጢአተኞችም ዋና እኔ ነኝ። ነገር ግን ክርስቶስ ኢየሱስ በእርሱ ለሚያምኑና የዘላለምን ሕይወት ለሚቀበሉ ወሰን የሌለው ትዕግሥቱን ከኀጢአተኞች ዋና በሆንሁት በእኔ እንደ ምሳሌ አድርጎ ያሳይ ዘንድ ምሕረትን አገኘሁ። እንግዲህ ዘላለማዊ ለሆነው፣ ለማይሞተው፣ ለማይታየውና ብቻውን አምላክ ለሆነው ንጉሥ ከዘላለም እስከ ዘላለም ክብርና ምስጋና ይሁን፤ አሜን። 1 ጢሞቴዎስ 1:15-17 NASV

የክርስቶስ ሥቃይ በእኛ ላይ የመብዛቱን ያህል መጽናናታችንም በክርስቶስ በኩል ይበዛልናል።
2 ቆሮንቶስ 1:5 NASV

በርግጥም በክርስቶስ ኢየሱስ በእውነተኛ መንፈሳዊ ሕይወት መኖር የሚወዱ ሁሉ ይሰደዳሉ።
2 ጢሞቴዎስ 3:12 NASV

ክርስቲያን በመሆኑ መከራ ቢደርስበት ግን ስለዚህ ስም እግዚአብሔርን ያመስግን እንጂ አይፈር፤
1 ጴጥሮስ 4:16 NASV

በክርስቶስ ወደ ዘላለም ክብሩ የጠራችሁ የጸጋ ሁሉ አምላክ፣ ለጥቂት ጊዜ መከራ ከተቀበላችሁ በኋላ እርሱ ራሱ መልሶ ያበረታችኋል፤ አጽንቶም ያቆማችኋል። 1 ጴጥሮስ 5:10 NASV

[19]

“ከእናንተ አንድ ሰው ሕንጻ ለመሥራት ቢፈልግ፣ መደምደም መቻል አለመቻሉን በመጀመሪያ ተቀምጦ ዋጋውን የማይተምን ማን ነው? መሠረቱን ጥሎ መደምደም ቢያቅተው፣ ያዩት ሁሉ ይዘባበቱበታል፤ እንዲህም ይላሉ፤ ‘ይህ ሰው ማነጽ ጀምሮ ነበር፤ መደምደም ግን አቃተው።’
ሉቃስ 14:28-30 NASV

እንደዚሁም፣ ከእናንተ ማንም ያለውን ሁሉ የማይተው፣ ደቀ መዝሙሬ ሊሆን አይችልም።
ሉቃስ 14:33 NASV

[20]

“መንግሥተ ሰማይ በዕርሻ ውስጥ የተደበቀ ሀብት ትመስላለች፤ አንድ ሰው ባገኛት ጊዜ መልሶ ሸሸጋት፤ ከመደሰቱም የተነሣ ሄዶ፤ ያለውን ሁሉ በመሸጥ ያንን የዕርሻ ቦታ ገዛ። “እንዲሁም መንግሥተ ሰማይ ውብ ዕንቍ የሚፈልግ ነጋዴ ትመስላለች፤ እጅግ ውድ የሆነ ዕንቍ ባገኘም ጊዜ ሄዶ ያለውን ሁሉ ሸጦ ገዛው። ማቴዎስ 13:44-46 NASV