የሚኖሩት አንድ ጊዜ ብቻ ነው
አንዳንድ ሰዎች “የሚኖሩት አንድ ጊዜ ነው” ይላሉ፡፡ አዎ፣ በምድር ላይ በህይወት በሚኖሩበት ጊዜ ለዚህም ነው እግዚአብሔርን ማወቅዎ በትክክል በጣም አስፈላጊ የሆነው!
ዘላለማዊ ፍጡሮች
በእርግጥ በምድር ላይ አንድ ጊዜ ብቻ ነው የምንኖረው፡፡ ነገር ግን ከዚህ ህይወት በኋላ ነው ለፍርድ የምንቀርበው [1]
ከዚህ ህይወት በኋላ ከእግዚአብሔር ጋር ለዘላለም ለመኖር ወይም ላለመኖር [2] የሰው ልጆች ዘላለማዊ ፍጡር ናቸው፡፡
ከዚህ ህይወት በኋላ ፍርድ ቢመጣ [3] ይህ ጥያቄ ይነሳል
እንዴት ፃድቅ፣ ታማኝ፣ ንፁህ ሆነን በእግዚአብሔር ፊት እንቆማለን[3] ?
በጣም አስፈሪው እና ትክክለኛው መልስ ግን መሆን አንችልም ነው፡፡ ማንም በህይወቱ የማይሳሳት የለም፡፡ በቅዱሱ እና ፍፁም በሆነው በእግዚአብሔር አይኖች ትንሿ እንኳን ስህተት ወይም ወንጀል ንፁህ አያደርጉትም፡፡ እግዚአብሔርን መተው እና በእርሱ ያለማመን እንኳን ዋናው ችግር ነው[5]፡፡ ውጤቱም በእነዚህ ሁሉ ነገሮች እና በህይወትዎ ሠርተውት በነበረ ስህተት ምክንያት ገነትን ማጣት እና የዘላለም ጊዜዎን በአስፈሪ ቦታ በማሳለፍ ከእግዚአብሔር ውጪ አሰቃቂ የወደፊት ህይወት ብቻ በመምራት የሚጠፉ ሲሆን ከዚህ በፊት እርስዎ [6]….
አስፈሪ ነገር?
አቁሙ! ይጠብቁ!…
ይህ አስፈሪ መሆኑን ወይም የሻይ ሲኒ አለመሆኑን እንደሆነ እያሰቡ ከሆነ…ማንበብዎን ይቀጥሉ ተስፋ እና የምስራች ስለሚኖር! በግል ማምለጫ መንገድ ስለሆነው ያንብቡ[7]
[1]
ሰው አንድ ጊዜ ሊሞት ከዚያም በኋላ በፍርድ ፊት ሊቆም ተወስኖበታል። ዕብራውያን 9:27 NASV
ዓለምን በጽድቅ ይዳኛል፤ ሕዝቦችንም በፍትሕ ይገዛል። እግዚአብሔር ለተጨቈኑት ዐምባ ነው፤ በመከራም ጊዜ መጠጊያ ይሆናቸዋል። መዝሙር 9:8-9 NASV
እርሱ ይመጣልና በእግዚአብሔር ፊት ይዘምራሉ፤ በምድር ላይ ሊፈርድ ይመጣል፤ በዓለም ላይ በጽድቅ፣ በሕዝቦችም ላይ በእውነት ይበይናል። መዝሙር 96:13 NASV
እነዚህ በእግዚአብሔር ፊት ይዘምሩ፤ እርሱ በምድር ላይ ሊፈርድ ይመጣልና፤ በዓለም ላይ በጽድቅ፣ በሕዝቦችም ላይ በእውነት ይበይናል። መዝሙር 98:9 NASV
ከዚህ በኋላ ታላቅ ነጭ ዙፋንና በእርሱም ላይ የተቀመጠውን አየሁ። ምድርና ሰማይ ከፊቱ ሸሹ፤ ስፍራም አልተገኘላቸውም። ሙታንን፣ ታላላቆችንና ታናናሾችን በዙፋኑ ፊት ቆመው አየሁ፤ መጻሕፍትም ተከፈቱ። ሌላም መጽሐፍ፣ እርሱም የሕይወት መጽሐፍ ተከፈተ፤ ሙታንም በመጻሕፍቱ ተጽፎ በተገኘው መሠረት እንደ ሥራቸው መጠን ተፈረደባቸው። ራእይ 20:11-12 NASV
እግዚአብሔር ጻድቅ ዳኛ ነው፤ ቍጣውንም በየዕለቱ የሚገልጥ አምላክ ነው። መዝሙር 7:11 NASV
መከራን ለተቀበላችሁት ለእናንተም ሆነ ለእኛ ደግሞ ዕረፍት ይሰጠናል። ይህም የሚሆነው ጌታ ኢየሱስ በሚንበለበል እሳት ከኀያላን መላእክት ጋር ከሰማይ በሚገለጥበት ጊዜ ነው። በዚያ ጊዜ እግዚአብሔርን የማያውቁትንና ለጌታችንም ለኢየሱስ ወንጌል የማይታዘዙትን ይበቀላል። እነርሱም ከጌታ ፊትና ከኀይሉ ክብር ተወግደው በዘላለም ጥፋት ይቀጣሉ፤ የሚቀጡትም በቅዱሳኑ ዘንድ ሊከብርና በሚያምኑበትም ሁሉ ዘንድ ሊገረም በሚመጣበት በዚያን ቀን ይሆናል፤ እናንተም ከሚያምኑት መካከል ናችሁ፤ ምስክርነታችንን ተቀብላችኋልና። 2 ተሰሎንቄ 1:7-10 NASV
አብ በማንም ላይ አይፈርድም፤ ነገር ግን ፍርድን ሁሉ ለወልድ አሳልፎ ሰጥቶታል፤ ይኸውም፣ ሁሉ አብን እንደሚያከብሩ ወልድን ያከብሩት ዘንድ ነው፤ ወልድን የማያከብር፣ የላከውን አብንም አያከብርም። ዮሐንስ 5:22-23 NASV
በመረጠው ሰው አማካይነት በዓለም ላይ በጽድቅ የሚፈርድበትን ቀን ወስኖአልና፤ እርሱንም ከሙታን በማስነሣቱ ለሰዎች ሁሉ ይህን አረጋግጦአል።” ሐዋርያት ሥራ 17:31 NASV
[2]
በምድር ዐፈር ውስጥ ካንቀላፉት ብዙዎች ይነቃሉ፤ አንዳንዶቹ ለዘላለም ሕይወት፣ ሌሎቹም ለውርደትና ለዘላለም ጉስቍልና ይነሣሉ። ዳንኤል 12:2 NASV
ሥጋን መግደል እንጂ ነፍስን መግደል የማይችሉትን አትፍሩ፤ ይልቁንስ ነፍስንና ሥጋን በገሃነም ማጥፋት የሚቻለውን ፍሩ። ማቴዎስ 10:28 NASV
ነገር ግን መፍራት የሚገባችሁን አሳያችኋለሁ፤ ከገደለ በኋላ ወደ ገሃነም ለመጣል ሥልጣን ያለውን እርሱን ፍሩት፤ አዎን፤ እርሱን ፍሩት እላችኋለሁ። ሉቃስ 12:5 NASV
ክፉዎች ተመልሰው ወደ ሲኦል ይወርዳሉ፤ እግዚአብሔርን የሚዘነጉ ሕዝቦችም ሁሉ እንደዚሁ። ችግረኞች ግን መቼም ቢሆን አይረሱም፤ የድኾችም ተስፋ ለዘላለም መና ሆኖ አይቀርም።
መዝሙር 9:17-18 NASV
“ከዚያም በግራው በኩል ላሉት ደግሞ እንዲህ ይላቸዋል፤ ‘እናንተ የተረገማችሁ፤ ለዲያብሎስና ለመላእክቱ ወደ ተዘጋጀው የዘላለም እሳት ከእኔ ተለይታችሁ ሂዱ፤ ማቴዎስ 25:41 NASV
“እነዚህም ወደ ዘላለም ፍርድ፣ ጻድቃን ግን ወደ ዘላለም ሕይወት ይሄዳሉ።” ማቴዎስ 25:46 NASV
ከዚያም በኋላ ሞትና ሲኦል ወደ እሳት ባሕር ተጣሉ፤ የእሳቱ ባሕር ሁለተኛው ሞት ነው። ስሙ በሕይወት መጽሐፍ ተጽፎ ያልተገኘ ሁሉ ወደ እሳት ባሕር ተጣለ። ራእይ 20:14-15 NASV
“ወጥተውም በእኔ ላይ ያመፁትን ሰዎች ሬሳ ያያሉ፤ ትላቸው አይሞትም፤ እሳታቸው አይጠፋም፤ ለሰውም ዘር ሁሉ አስጸያፊ ይሆናሉ።” ኢሳይያስ 66:24 NASV
[3]
‘ሥጋ ለባሽ ከእግዚአብሔር ይልቅ ጻድቅ ሊሆን ይችላልን? ሰውስ ከፈጣሪው ይልቅ ንጹሕ ሊሆን ይችላልን? ኢዮብ 4:17 NASV
[4]
ትክክለኛውን ነገር የሚያደርግና ፈጽሞ ኀጢአት የማይሠራ፣ ጻድቅ ሰው በምድር ላይ የለም።
መክብብ 7:20 NASV
ስወለድ ጀምሮ በደለኛ፣ ገና እናቴም ስትፀንሰኝ ኀጢአተኛ ነኝ። መዝሙር 51:5 NASV
ጻድቅ ብሆንም እንኳ፣ ልመልስለት አልችልም፤ ዳኛዬን ምሕረት ከመለመን ሌላ ላደርግ የምችለው የለም። ኢዮብ 9:15 NASV
“ከፍ ባሉት ላይ ለሚፈርድ አምላክ፣ ዕውቀትን ሊያስተምረው የሚችል አለን? ኢዮብ 21:22 NASV
[5]
በእርሱ የሚያምን ሁሉ አይፈረድበትም፤ በእርሱ የማያምን ግን በአንዱ በእግዚአብሔር ልጅ ስም ስላላመነ፣ አሁኑኑ ተፈርዶበታል። ዮሐንስ 3:18 NASV
[6]
“በጠባቡ በር ግቡ፤ ወደ ጥፋት የሚወስደው መንገድ ትልቅ፣ በሩም ሰፊ ነውና፤ ብዙዎችም በዚያ ይገባሉ። ወደ ሕይወት የሚያደርሰው ግን መንገዱ ቀጭን፣ በሩም ጠባብ ነው፤ የሚገቡበትም ጥቂቶች ብቻ ናቸው። ማቴዎስ 7:13-14 NASV
“ወጥተውም በእኔ ላይ ያመፁትን ሰዎች ሬሳ ያያሉ፤ ትላቸው አይሞትም፤ እሳታቸው አይጠፋም፤ ለሰውም ዘር ሁሉ አስጸያፊ ይሆናሉ።” ኢሳይያስ 66:24 NASV
የመስቀሉ ቃል ለሚጠፉ ሞኝነት ነው፤ ለእኛ ለምንድ ነው ግን የእግዚአብሔር ኀይል ነው፤ 1 ቆሮንቶስ 1:18 NASV
ወንጌላችን የተከደነ ቢሆን እንኳ፣ የተከደነው ለሚጠፉት ነው። የእግዚአብሔር አምሳል የሆነውን የክርስቶስ፣ የክብሩን ወንጌል ብርሃን እንዳያዩ፣ የዚህ ዓለም አምላክ የማያምኑትን ሰዎች ልቡና አሳውሮአል። 2 ቆሮንቶስ 4:3-4 NASV
አንዳንድ ሰዎች የዘገየ እንደሚመስላቸው ጌታ የተስፋ ቃሉን ለመፈጸም አይዘገይም፤ ነገር ግን ማንም እንዳይጠፋ ፈልጎ፣ ሁሉ ለንስሓ እንዲበቃ ስለ እናንተ ይታገሣል። 2 ጴጥሮስ 3:9 NASV
ምስክርነቱም ይህ ነው፤ እግዚአብሔር የዘላለምን ሕይወት ሰጠን፤ ይህም ሕይወት ያለው በልጁ ነው። ልጁ ያለው ሕይወት አለው፤ የእግዚአብሔር ልጅ የሌለው ሕይወት የለውም። 1 ዮሐንስ 5:11-12 NASV
“በእርሱ የሚያምን ሁሉ የዘላለም ሕይወት እንዲኖረው እንጂ እንዳይጠፋ እግዚአብሔር አንድያ ልጁን እስከ መስጠት ድረስ ዓለምን እንዲሁ ወዶአልና፤ ዮሐንስ 3:16 NASV
[7]
“እውነት እላችኋለሁ፤ ቃሌን የሚሰማ፣ በላከኝም የሚያምን የዘላለም ሕይወት አለው፤ ከሞት ወደ ሕይወት ተሻገረ እንጂ ወደ ፍርድ አይመጣም። ዮሐንስ 5:24 NASV
እነርሱም፣ “ታዲያ የእግዚአብሔርን ሥራ ለመሥራት ምን ማድረግ አለብን?” አሉት። ኢየሱስም፣ “እርሱ በላከው ታምኑ ዘንድ፣ ይህ የእግዚአብሔር ሥራ ነው” ሲል መለሰላቸው።
ዮሐንስ 6:28-29 NASV
የላከኝም ፈቃድ፣ ከሰጠኝ ሁሉ አንድ እንኳ ሳይጠፋብኝ በመጨረሻው ቀን እንዳስነሣ ነው። የአባቴ ፈቃድ ወልድን አይቶ በእርሱ የሚያምን ሁሉ የዘላለም ሕይወት እንዲኖረው ነው፤ እኔም በመጨረሻው ቀን አስነሣዋለሁ።” ዮሐንስ 6:39-40 NASV